AMHARIC PAGE

ኤችአይቪ ፖዘቲቨ እና ነፍሰጡር ከሆንኩ የፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶች Anti-HIV Medications መጀመር
አለብኝ ወይ?

ኤችአይቪ መድሃኒት መጀመር ያለበት:-

  • ከኤችአይቪ ጋር የተያያዘ የተለያዩ አይነት ከባድ የሕመም ስሜቶች ከተሰሙ severe symptoms
    ወይም የኤድስ ደረጃ ደርሰው ከነበር

  • የሲዲፎር ሴል ቁጥር (cd4 count) 200 cells/mm3 ወይም በታች ከሆነ (350 cells/mm3 ወይም በታች ሲሆን
    ኤችአይቪ መዳሃኒት መጀመር ይገባል)

  • የቫይረሱ ብዛት (viral load) 1,000 copies/mL በላይ ከሆነ

በተጨማሪ የኤችአይቪ መድሃኒት መውሰድ ተገቢ የሚሆንበት ምክንያት
(mother-to-child transmission) በፅንስ ጊዜ
ኤችአይቪ ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለመከላከል ነው። ኤችአይቪ ከአናት ወደልጅ አንዳይተላለፍ የተወሰኑ
የሕክምና የመዳኒት አይነቶች በዝርዝር ከታች ተገልፃል።

ነፍስጡር ከሆንኩና ወይም ለማርገዝ እቅድ ካለኝ ምን አይነት መዳኒት ላይ ነው መሆን አለብኝ?

አንድ እናት እርጉዝ ከሆነች ወይም ለማርገዝ የምታስብ ከሆነ የራስዋንና የልጅዋን ጤና ለመጠበቅ ስትል የኤችአይቪ
መዳኒት መውሰድ ጥቅሙን እና ጉዳቱን መረዳት ይኖርባታል።
አንዳንድ የኤችአይቪ መዳኒቶች እንደ ሳስቲቫ
(such as Sustiva) አይነት በፍጹም መወሰድ የለበትም ምክንያቱም
በፅንስ ግዜ የተበላሽ ፅንስ ስለሚፈጠር በተለይ በመጀመሪያ እርግዝና አካባቢ ከተውሰደ። አንድ እናት ከማረገዝዋ በፊትም
ሆነ በእርግዝናዋ ጊዜ ከዶክተርዋ ጋር በቅርብ በመነጋገር ለእናትና ለልጅዋ ተስማሚ የሆነውን መድሐኒት አብረው መወሰን
ይኖርባቸዋል።

ነፍስጡር እናት ከምትወስዳቸው የኤችአይቪ መድሃኒት ውስጥ
AZT ሶስቱ ክፍሎች (three-part AZT (also known as
Retrovir, zidovudine, or ZDV)
መኖር የገባል ኤችአይቪ ቫይረስ ከናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በጣም ትልቅ
አስተዋጾኦ የሚያደርግ መዳኒት ነው።

የኤችአይቪ መድሐኒት በመውስድ ላይ እገኛለሁ እና የኤችአይቪ መድሐኒቴን መለውጥ ያስፈልገኛል?

የኤችአይቪ መድሐኒት በመውስድ ላይ የምትገኝ እናት ከዶክተርዋ ጋር ካለማቁዋረጥ በመነጋገር ጥቅሙንና ጉዳቱን
በመረዳት መዳኒቱን በትክክል በመውሰድ የመዳኒቱን መጠን በትክክል አስተካክሎ መውሰድ ጠቃሚ ነው።
ከታች የተዘረዘሩት መዳኒቶች በነፍስጡር እናት መወሰድ የሌለባቸው ናቸው፦
·      Hivid® (Zalcitabine)
·        Rescriptor® (Delavirdine) mg
·        Efavirenz (Sustiva®)
·        D4T (Zerit®) for pregnant women who haven't used any HIV drugs before
·        Combination of ddI and d4T (Videx® and Zerit®)
·        Oral liquid of amprenavir (Agenerase®)
·        Hydroxyurea (anticancer drug) during the first semester

ምንድን ናቸው እንዝህ ሶስት ክፍል AZT Regimen?

  1. ኤችአይቪ ፖዘቲቨ ነፍሰጡር ሴት ከ14-34 ሳምንት ውስጥ AZT መውሰድ አለባት። በቀን አምስት ጊዜ 100
    mg  የሚወሰድ አለ ወይም በቀን ሶስት ጊዜ 200 mg ወይም ደሞ በቀን ሁለቴ 300 mg መውሰድ ይቻላል።
  2. በምጥ እና በወሊድ ግዜ ለእናት AZT በአይቪ በቬንዋ ይሰጣታል። (through an IV in the vein)
  3. ሕፃኑ ከተወለደ በሃላ AZT በፈሳሽ መልክ ይሰጣል፡፡ የሚሰጠው በየሰድስት ሰዓቱ ሲሆን ለስድስት ሳምንት ነው።

ልጄ ኤችአይቪ ፖዘቲቨ ሆኖ ነው ወይ ይሚወለደው?

ማንም ሰው በእርግጠኛነት የሚወለደው ልጅ ኤችአይቪ ፖዘቲቨ ሆኖ ይወለዳል ወይ ኤችአይቪ ነጌቲቨ ሆኖ ይወለዳል ብሎ
መናገር ባይችልም ግን ይህ የAZT ሶስት ክፍል መዳኒት ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በጣም ትልቅ ሚና
የሚጫወት መዳኒት ሲሆን በ70% ቫይረሱ እንዳይተላለፍ አስተዋጾኦ ይደርጋል።
ሌላው መደርግ ይሚገባው ቅድመ ጥንቃቄ በፅንስ ግዜ የሕክምና ክትትል ማድረግ በጣም አስፈላጊና ጠቃሚ ነው እንዲሁም
የኤችአይቪ  ።



ለበለጠ ለመረዳት ዶክተሮን ያነጋግሩ ወይም
በአካባቢዎ የኤድስ ሆትላይን መደወል ይችላሉ።









This article was provided by AIDSinfo.  
Translated from thebody.com HIV and pregnancy. Oct 2007
F
rom English To Amharic translation by Abesha Care Team


This information is based on the U.S. Department of Health and Human Services' Recommendations for Use
of Antiretroviral Drugs in Pregnant HIV-1-Infected Women for Maternal Health and Interventions to Reduce
Perinatal HIV-1 Transmission in the United States (available at http://aidsinfo.nih.gov).
© 2007 Abesha Care Inc.  All Right Reserved. office@abeshacare.org
እርግዝና እና ኤችአይቪ