.....የቀጠለ
አጋጣሚ ሆኖ የሁለታችን እዛ መገጣጠም፤ ሁለታችንም አበሾች መሆናችን፤ የሰራችን ባሕሪ በመመሳሰል
ሌሎችም ሌሎችም ነገሮች አሰተዋጾ ያድርገው ስናወራም ስንስቅም ስንጨዋውትም በጣም በጣም ከመጠን በላይ
ተዋሃድን። ይህ ሁሉ አስተዋጾ አድርጎ ለመጋባተ በቃን። አሁንስ አልተቸገርኩም ለባለቤቴ ለመንገር ቫይረሱ
እንዳለብኝ ምክንያቱም እሱም ከቫይረሱ ጋር የሚኖር በጣም ጠንካራ እና በጣም የሚወደኝ የሚያስብልኝ ሰው
ሰልሆነ። እኔና ባለቤቴም የሁለት አመት ወንድ ልጅ ወልደናል። በጣም ደስተኛና በጣም ቢዚ የሆነ ኑሮ የምኖር
ሴት ስሆን። ልጄም በጣም ጤነኛና ዕለት በዕለት ደስታን የሚሰጠኝ ከእግዛብሔር የተሰጠኝ ጸጋ ነው።

ባላችሁበት ቁጭ ብላችሁ የምታነቡ፡ ያለፈው ትዳሬ ጥሩ ስላልነበረ እኔ ማዘን አለብኝ ለምትሉ ሰዎች ውይ ደሞ
ቫይረሱ ስላለብን እንደማንኛውም ሰው መኖር አንችህልም ብላችሁ የምታስቡ ሰዎች እራሳችሁን ከሕብረተሰቡ
የምታገሉ ሁሉ ይሄን አስተሳሰብ ወደሁላ ትታችሁ በጣም ይገባኛል ከባድ እንደሆን በስደት ላይ ሆኖ ከቫይረሱ
ጋር መኖር ግን እናተ አሸናፊዎች ናችሁ ኤይች አይቪ አያሽንፋችሁም።
ሁልጊዜ ወደፊት በማሰብ ከጨለማ ይልቅ ብርሃን ስላለ ሕይወታችን ወደብርሃን እንምራት። በሕይወታችን
ስንኖር ምርጫው የኛው ነው መደሰት ወይ ማዘን? ግልጽ ሆኖ የተቀመጠ ነገር ነው መደሰት የፈልገ ሰው
ይጥራል ሳይሰለች ደስታን ለማግኝተ፡ ሕይወቱ ውስጥ ብርሃን ለማስገባት ወይ ደሞ እያዘነ በጨለማ ይኖራል።
ምርጫው በእጃችን ነው። የወጫዊ አካላችን አይደለም ማንነታችህንን የሚገልጸው ምግባራችን እንጂ።

ወደራሴ ስመለስ መቸም አንድ ቀን ትዝ አይለኝም ሳልደሰት ያደርኩበ ቀን። እራሴንም ከሌላው ሰው ያሳነስኩበት
ቀንም ትዝ አይለኝም። በስራዬም ሆነ በኑሮዬ በጣም ደስተኛ ነኝ።
አንድ ነገር ግን አለ ልንክደው የማይገባ ዕውነታ ሕብረተሰባችን ይህን በሽታ እንደማንኛወም በሽታ የማይቀበለው
በመሆኑ ኤይች አይቪ ፕዘቲቪ የሆኑ ሰዎች ስለሚገለሉ በስነ ልቦናቸው ላይ በጣም ከፈተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው
መሆኑን እናውቃለን። ኤይች አይቪ ፕዘቲቪ የሆኑ ሰዎች ሁሉ መውጣት አለባቸው ማለት አስቸጋሪ ሲሆን ግን
ወተው እራሳቸውን መስዋት አርገው የሚያስተምሩንን ደሞ እንደግፋቸው። አናግላችው አንጠቓቐምባችው። አንድ
በራሴ የደረሰ የማስታውሰው ነገር ልንገራችሁ የሰርጌ ዕለት ነበር እና በደስታው በሆካታ መካከል እኔ ሆዬ በሃሳበ
ነጎጄ እስቲ አሁን በተሰበሰበው ሰው መሃል ተነስቼ መናገሪያውን ይዥ እኔ ኤችአይቪ ፕዘቲቪ ነኝ ብዬ ብናገርስ
እና እንዴት ደስተኛ እንደሆንኩ ዛሬ የደስታዬ ተካፋይ መሆናችውን አመስግኜ ቁች ብልስ? እያልኩ ከራሴ ጋር
ስማገት
ግን እስቲ አስቡት ለእኔና ለባለቤቴ በጣም ቀላለ ነገር ነበር ዕውነታውን መጋፈጥ ግን ሁልግዜ እንደዚህ አይነት
ነገር ሲያጋጥም ማሰብ ያለብን አብረውን ያሉትን ሰዎች ምን ያህል እንደሚጎዳ ሰናሰበው ለሚወዱን
ለቤተሰቦቻችን ብለን ዝምታን መርጥን።
ዋናው የጽሁፌ መነሻና መንደርደሪያ ሁላችንም በዚህ አለም ስንኖር ኤችአይቪ ፕዘቲቪ ሆንን አልሆንን እኛ
ሰዎች በሕይወታችን ላይ የተለያዩ ፈተናዎች ያጋጥሙናል። እንግዲ ስንቶቻችን ነን ፈተናውን አልፈን
ሕይወታችንን በድል አድራጊነ የምንኖራት?
እግዛብሔር በያለንበት ፍቅርና ሰላሙን ያብዛልን እያልኩ በዚህ እሰናበታችሁሃለው።
የናነተው እህት
ሰላም
Name:
Nick name
Email Address:
(optional)
Comments, or feedback:
ለመመለስ / Back
ያስተምራል ወይም
ለሌላሰው ምሳሌ ይሆናል
ብላችሁ የምትሉትን
ታሪክ ጻፉልን በደስታ
ለንባብ እናበቃቸዋልን
AMHARIC PAGE
© 2007 Abesha Care Inc.  All Right Reserved. office@abeshacare.org