ምን ይሻላል? ምን ይበጅኛል? ፍቅር የሚያወቀው ያውቀዋል ምን እንደማረግ ግራ ገባኝ። እስቲ እናተ ንገሩኝ በኔ ቦታ
ብትሆኑ ምን ታረጋላችሁ ጥያቄዬን ለናንተ ጣል አርጌ ልለፍ። ምን ላድርግ?
ትክክልኛ ምላሽ ይኖረው ይሆን?

በጣም ስለወደድኩት ነው እጂ በጣም ብዙ ግዜ ሞክሬአለሁ ልርቀው፤ ልሸሸው ዋናው ጉዳዩ ግን እዚህ ላይ ነው። አሁን
የማቀውን ያኔ ባቅ ኖሮ ታሪኩ ሌላ ነበር። ግን በውቅቱ ትክክል ነው ብዬ ያመንኩትን ፈጸምኩ ማለትም በጣም ፍቅራችን
እይጸና በመምጣቱ ልነግረው ወሰንኩ እንግዲ እንዲህ ስል ግን በጣም ከብዶኝ እንደንበረ ልትዘንጉት አይገባም።

ስነግረው በጣም የሚገርመኝ ነገር እስታሁን የማደንቀው በጥሩ ነበር የተቀበለው። ብዙ የማያቃቸው ነገሮች የማቃትን ያህል
አስተምረው ነበር። ብዙ ኢንፎርሜሽን በማንበብ ብዙ ተምረናል አብረንም። ግን ይህን ለማረግ በሁለታችንም መካከል
በጣም ብዙ ትግስት የሚጠይቅ ስራ ነበር። እራስንም በዛ ሰው ቦታ ላይ አርጎ መመልከትም ያስፈልግ ነበረ።

ከሱ ጋር እንደማንኛውም ሰው ጥሩ የፍቅር ግዜያቶች አሳለፍን ግን በዛው መጠን ብዙ የማንግባባችው እና የማንስማማበት
ነገሮች ነበሩ። ለምሳሌ ያህል አንድ ጣል ላርግ ለሎች እህቶቼም ይጠቅማል ብዬ ስለማስብ። የትዳር እና የልጅ ነገር ሲነሳ
በጣም ይፈራል። በደንብ በግልጽ የተነጋገርንባቸው ጉዳዬች ነገሩ (ጤነኛ ልጅ ባይወለጅስ፤ ብትታመሚና ብትሞችስ፤ ልጁ
ያለናት ሊያድግ ነው ውይ የሚሉት ጥያቄዎችን በማንሳት አንደኛ፡ ጭንቅላቴን አዞረው ሁለተኛ፡ በጣም ሞራል ይሚነኩ
ነገሮች ነበሩ ለኔ በዛ ግዜ ከሱ ጋር እንዳልቀጥል ያረገኙ ዋነኛ ምክንያቶቹ እንዚህና የመሳሰሉት ነበሩ።) በጣም ከባድ ግዜ
ነበር ለሁለታችንም የመለያያው ቀን ሲደርስ። ግን ሁሌ የሰው ልጆች ሆነን የማንገነዘበው ነገር በሕይወታችን መጥፎ ነገር
ሲደርስብን ውይም የእዚህን አለም መከራና ችግርን ሲፈራርቁብን ይህን ሁሉ አሽንፈን በድል አድራጊነት ስንወጣ ነው
የተሳካ ሕይወት ኖርን የሚባለው። “በእሳት የተፈተነ ወርቅ እንደሚባለው አባባል” ያ መጥፎ ግዜ ከሱ ጋር ያሳለፍኩት
ያለመግባባትና ያለመስማማት እንደማንኛውም የሕይወት መሰናክልና የትምህርት መቅስሚያ ግዜያቶች ነበሩ ብዬ አልፋቸዋለሁ።

ከሱ ከተለየሁ ብዙም ሳልቆይ ከባለቤቴ ጋር በዚህ አጋታሚ ልገልጽ የምፈልገው ነገር መጻፍ በጣም እወዳለሁ እና ልክ እኔ
ያለፍኩትን ሕይወት የምትኖሩ እህቶችም ሆነ ወንድሞች ካላችሁ ሁሌ ዕድሉ ክፍት ነው በቻ ከኛ የሚጠበቀው ተስፋ
አለመቁረጥ እና ተስፋሳይቆርጡ ከመሞከር ወደሃላ አለማለት። ከባለቤቴ ጋር የተዋወኩት እዚህ የፍረንጆች ፎረም ላይ ነው
ስለዚህ ጉዳይ ስጽፈ ስለ “HIV” አንድ ቀን በአጋጣሚ ጠየቀኝ ኬት እንደሆንኩ እኔም ነገርኩት ኢትዬጵያዊ መሆኔን
በጣም ገረመው፤ አጋጣሚው። እሱም ሲነግረኝ ትንሽ ተጠራጥሮ እንደነበር (በኒክ) ስሜ። እኔም አሁን ሳስበው በጣም
ግርም ይለኛል አጋጣሚው....
Real Story Real People!
ተስፋ
ይቀጥላል
ይቀጥላል
ላም ለሁላችሁ ይሁን ብዬ ወደዋናው ሃሳቤ ልግባ
ዕድሜዬ ሰላሳ አምስት አመት ሲሆን ዛሬ ሓሳቤን ልጽፍ ያነሳሳኝ የዛሬ አስር አመት አካባቢ ይህን አይነት አድል
አለመኖሩ ልበለው ወይስ ሰዎች ለቫይረሱ ያለችው አስተሳሰብ አላደገም ነበር ልበል ብቻ በዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ
ላይ ሳንነጋገር አንድ ምዕተ አመት በማለፉ፤ በዚህ አጋጣሚ ይህንን መድረክ የከፈቱልንን ሰዎች ሳላመሰግን ማለፍ
አልፈልግም፤ በቀጠልም የኔ የራሴ እውነተኛ ታሪክ ሌላውን ያስተምራል ብሎም ተርፎም ለሌላው ሞራል ይሰጣል
ብዬ ስላመንኩ ታሪኬን ለመናገር ተገድጃለሁ። ኤችአይቪ እንዳለብኝ ያወኩት ወደ ውጭው አለም ለትምህርት
ከመጣሁ በሃላ ባደረኩት የደም ምርመራ ነው። ምርመራውን ያደረኩት ታምሜ ወይም ደሞ እራሴን ተጠራጥሬ
አልነበረም እንግዲህ ልብ በሉ ይህን ስል በምንም አይነት ይሄ ቫይረስ ይይዘኛል ብዬ እራሴን ተጠራጥሬ አላቅም
ነበር እንግዲ ስንቶቻቹሁ ናችሁ ተጠራጥራቹ የያዛችሁ? ወይ ደሞ ስንቶቻችሁ ናችሁ ተጠራጥራችሁ ያልያዛችሁ?
ይህንን ምላሽ ለናተ ልተወውና ወደ ታሪኬ ላዝግም ትምህርቴን በምጨርስበት አካባቢ አንድ ሰው ተዋውኩ ይህ ማለት
የዛሬ አስር አመት አካባቢ ይሆናል። ያው የአገሬ ልጅ በጣም ጥሩ ሰው ነበር እና ስደት ላይ ያላችሁ ሰዎች
ታቁታላችሁ አንድ ሰው ስትተዋውቁ ከዛም ብሎም ተርፎም ያሰው በጣም ጥሩ ሲሆኑላችሁ መዋደዱ ይመጣል ፍቅሩ
ይጠነክራል። በኔና በእሱ መሃከልም እንግዲ ፍቕሩ መቀጣጠል ጀመረ። የፍቅሩ ነበልባል ለካ እኔን ብቻ አልነበረም
የለበለበኝ እሱም ኖርዋል ለካ። አብረን በፍቅር ቀለጥን ተዋሃድን ግን ግን አሁን እዚህ ጋር ሁላችሁም የምትጠይቁት
ጥያቄ አለ መቸም አይደል እንዴ?
AMHARIC PAGE
© 2007 Abesha Care Inc.  All Right Reserved. office@abeshacare.org