ከኤችአይቪ ቫይረስ እንዳለቦ ካወቁ እራስን አረጋግቶና ችግሩን እንደማንኛዉም የጤና ችግር በማየት ቫይረሱ የሚያስከትለውን
ጉዳት ለመቀነሰ እና ለመከላከል በሕክምና፣ በአመጋገብ፣ እንዲሁም በባህርይ ላይ አስፈላጊ የሆኑ ለውጦችን በማምጣት ጥሩ ሕይወት
መኖር ይቻላል። አንድ ሰው ኤችአይቪ አለበት ማለት አሁኑኑ ታሞ ይተኛል ወይም በቅርቡ ሕይወቱ ያልፋል ማለት አለመሆኑን
ማወቅ ተገቢ ነው። ከኤችአይቪ ፖዘቲቨ ከሆኑ በኅላ ሰዎች የፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶችን በመውሰድ ለረጅም ዓመታት ጤናማ ሆነው
ለመኖር ይችላሉ። አንዳንድ ሰዎች የበሽታዉ ምልክት ጨርሶ ሳይታይባቸው ከ15 ዓመት በላይ ከቫይረሱ ጋር መኖር ይችላሉ ይህም
ነው ቫይረሱ እንዲስፋፋ ያረገው አንዱ መንግድ። ኤችአይቪ ቫይረስ በደም ውስጥ በመኖሩ ምክንያት ሊሰማ የሚችል ስሜት
ይኖራል ለመጀመሪያ ግዜ አንድ ሰው ሲያቅ። ይህ ስሜት ቀስበቀስ እይተለወጠ ይመጣል። አንድ ሰው አውነታውን መቀበል መቻል
አለበት። ጥሩ ያልሆኑትን ስሜቶች ለማስወገድ ጥቃሚ መርኅ ይሆናሉ ያልናቸውን ከእናንት ጋር እናጋራ፦

ሁኔታዎች እያደር የተሻሉ እንደሚመጡ ተስፋ ማድረግ፦ ፈታኝ የሆነ ሰሜት ሲሰማ ይችላሉ ግን ሁሌ ከጊዜ ጋር እየተሻሻሉ
እንደሚሄዱ ማመን እና መቀበል። የተሻለ ሁኔታ እንደሚኖር ተስፋ የሚሰጡ ብዙ መንገዶች አሉ።
የሚወዱትን ነገር መስራት አላማቅም ለምሳሌ፡ መጻፍ ማንበብ ወይ ወደውሃ ቦታ ሄዶ መዝናናት አይምሮን አድሶ መምጣት
እና የተረጋጋ ህይወት ለመኖር መሞከር።
ከኤችአይቪ ፖዘቲቨ ከሆኑ ሰዎች ጋር መመካከር ወይም መመካከር ከፈልጉ በዚ ጉዳይ ላይ አበሮ የሚጉዋዝ ሰው ለማወቅ መሞከር
እና ለማወራት ለመመካከር መሞከር ወይንም support group ጋር በመሄድ የምክር እርዳታ ማግኘት ወይም online chat room
እንደ ''አበሻ HIV chat room'' ቦታዎች በመሄድ መወያየት መልካም ነው። እና ሁሌም የሚያስደስቶትን ነገሮች ከማድረግ
አለመቆጠብ። ያላገቡ ከሆነና ለትዳርም ሆነ የፍቅር ጓደኛ ከፈልጉ
www.abeshacare.com ላይ በመመዝገብ እና የሚመስሎትን ሰው
መተዋወቅ ይችላሉ።

የኀዘንና የብስጭት ሰሜቶችን ማስወገድ በጣም ጠቃሚ ነው።

አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፦ በዚህ ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ብርታትና ጥንካሬ ይሰጣል። የሰውነት እንቅስቃሴ በአሁኑ
ባለንበት ከፍለ ዘመን ትልቅ ሚና ይጫወታል ጤነኛ የሆን ሕይወት ለመምራት ይህ ለማንኛውም ሰው የሚሰጥ ምክር ነው።
ከስራ ደከሞ የዋለን ሰውነት በተለያየ የአካል እንቅስቃሴ ማዝናናት እንደ የእግር ጉዞ፣ ዋና፣ የተለያዩ የስፕርት ጨዋታዎችን
መጫወት በጣም ጠቃሚ ነው።

እራስን ማግለል፡ ዋነኛውና ትልቁ ችግር የሆነው በአሁን ግዜ ሰዎች በጣም እራሳችውን ያገላሉ እንዲሁም ሕብረተሰባችንም አለማወቅ
ኤችአይቪ ፖዘቲቨ የሆኑትን ሰዎች ያገላሉ ይህ መለወጥ ስላለበት ነው ለዛ ነው የቻት ሩሙ የተከፈተው እና ሕብረተሰባችንን
ማስተማር ገዴታ ያለብን። እንደማንኛውም ሰው ሥራን በመስራት፣ ዘመድ ወዳጆችን አለመራቅ እና የሚሆኖትን ጋደኛ በማፈራት ጥሩ
ነው።

ባለሞያን ማማከር፦ ስለ ኤችአይቪ/ኤድስ ቫይረስ ማውቅ መጠየቅ። አንድ ከኤችአይቪ ጋር የሚኖር ሰዉ የጭንቀት እና የመከፋት
ስሜት ካለቀቀው የህክምና ባለሞያዎች ወይንም አማካሪዎችን በስልክም ሆነ በአካል ማግኘትና ማማከር ያስፈልገዋል።

ያስታውሱ! ብቻዎን እንዳልሆኑ በአሁኑ ሰአት በአገር ውስጥ ይሁን ከአገር ውጭ ከኤችአይቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ብዙ ሰዎች
እንዳሉ ሁሉ በውጭ የሚኖሩት ሰዎች ብዛት ግምቱ ባይታውቅም በርካታ እንድሆን ይታመናል። በአገር ውስጥም ከ1.5 ሚሊዮን
በላይ የሚቆጠሩ ሰዎች ከቫይርሱ ጋር ይኖራሉ።

አንድ ኤችአይቪ ቫይረስ በደሙ ውስጥ ያለበት ሰው በቫይረሱ ለመያዝ ሆን ብሎ የሰራው ስህተት ስለሌለ ራሱን መውቀስ እና
መጨነቅ የለበትም። ማድረግ ያለበት ነገር ቢኖር ለሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች እንዳይጋለጥ ራሱን እንዲጠብቅ ትምህርት ማግኘት እና
ከኤችአይቪ ነፃ የሆኑ ሰዎች ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ ስብዓአዊነት ተስምቶት ቅድመ ጥንቃቄዎችን ማድረግና፣ ከተቻለም ማስተማር።
ከኤችአይቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸዉ አውቀው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያሉበትን የጤና ሁኔታ ተቀብለው
ራሳቸውን በማረጋጋት ወደፊት በተሻለ መንገድ ለመኖር ዕቅድ አውጥተው መኖር ማሰብ አለባቸው። እራሰን አረጋግቶ ለመኖር ከዚ
በታች የተጠቀሱት ጠቃሚ መመሪያዎች በዝርዝር ጠንቅቆ ማወቅ አጥጋቢ የሆነ የፀባይ እና የአኗኗር ለውጥ ለማምጣት ይረዳል፦

ኤችአይቪ ቫይረስ በደም ዉስጥ መኖሩን በታወቀበት ጊዜ ሊገጥም የሚችለውን የጭንቀት እና የፍርሃት ስሜት እንዲሁም የሰውንት
ለውጦች ሊመጡ ይችላሉ እንሱን ሁሉ ተቀብሎ ወደፊት ማሰብ እና መኖር
አንዳንዴ የሚመጡ የበሽታ ስሜቶችን ሲስሙ ወድያውኑ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ
የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ የራስን ንፅህና መጠበቅ እና የሰውነት እንቅስቃሴ የማድረግ አስፈላጊነትን፤
ጥንቃቄ ስለተሞላበት የግብረ ሥጋ ግንኙነት እና መውድ በሚፈለግበት ግዜ
ሴቶች ምን ማርግ እንዳልባቸው ማውቅ

ዕፅም ሆነ አልኮል በብዛት መውሰድ የሰውነትን የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም ያዳክማል። ጤናማ ሆኖ ለመኖርም ሆነ ጤንነትን
ለመንከባከብ አልኮልንም ሆነ ዕፅን መጠቀምን እስከመጨረሻው መተው አማራጭ መንገድ ቢሆንም ይህንን ሁሉም ሰው በቀላሉ
ሊያደርገው አይችልም። የሚወሰደው የሲጋራ፣ የዕፅ ወይም የአልኮል መጠንን በተቻለ መጠን መቀነስ ጤንነትን በተሻለ ሁኔታ
ለመጠበቅም ይረዳል።

ምን አይነት ምግብ መመገብ ለጤና ጥሩ የሆኑ የተመጣጠን ምግብ መመገብ ጠቀሜታውን የሚያብራራ ገጽ በቅርቡ ይመጣል
© 2007 Abesha Care Inc.  All Right Reserved. office@abeshacare.org
AMHARIC PAGE
ከኤችአይቪ ፖዘቲቨ ከሆኑ በኋላ ምን ማረግ ይገባል