Content Source:
Centers for Disease Control and Prevention
Divisions of HIV/AIDS Prevention
National Center for HIV/AIDS, Viral Hepatitis, STD, and TB Prevention
© 2007 Abesha Care Inc.  All Right Reserved. office@abeshacare.org
© 2007 Abesha Care Inc.  All Right Reserved. office@abeshacare.org


ኤችአይቪ ከህዩመን ኢምዩኖደፊሸንሲ ቫይረስ  Human Immunodeficiency Virus (HIV)  
የሰውነትን የበሽታ መከላከያ በተለይ የነጭ ደም ሴሎችን በማጥቃት በቀላሉ ሰውነት ለበሽታ
እንዲያጋልጥ ቫይረስ ነው
።  

ኤችአይቪ ያለባቸው ሰዎች የበሽታ ምልክት ሳይታይባቸው ለብዙ አመታት መኖር ይችላሉ። ቫይረሱ
በሰውነት ውስጥ እስከ አስር ዓመት በመቆየት ምንም ሳይታወቅ ምንም አይንት የህመም ምልክት
የማያሳዩ ሰዎች ከመኖራቸውም በላይ በአሁኑ ሰዔት ቫይረሱ ሳይታወት ከአንድ ሰው ወደሌላ ሰው
በፍጥነት እይተተላለፈ ይገኛል። ኤችአይቪ ያለባቸው ሰዎች ተገቢውን ሕክምና በማድርግ መድሐኒት
የሚወስዱ ከሆነ ወይም መዳኒት ያልጀመሩም ከሆኑ ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ የተመጣጠነ
ምግብ በመመግብና መጠነኛ የሰውንት እንቅስቃሴ በማድረግ እንደማንኛውም ሰው መኖር ይችላሉ።
እራስን አለማግለልና የአዕምሮ ጭንቀት ማስወገድ ከያንዳንዱ ሰው የሚጠበቅ ነው። ሕብረተሰባችንም
ቢሆን ከቫይርሱ ጋር የሚኖሩትን ሰዎች ማግለል እንደሎለብን መረዳት ይኖርበታል። ይሄን ስል
ማግለል የለብንም ብሎ መስበክ ወይም መናገር ብቻ ሳይሆን በዕለት ዕለት ኑሮአችን ላይ በተግባር
ማዋል እንዳለብን መረዳት በጣም ጠቃሚ ነው። ይህ የሰውን የማግለል ባህሪ እኛን የአበሻን የጎዳና
በመጉዳት ላይ ያለ ስለሆንም ይህ
ጎጂ-ባሕል መወገድ አለበት። ስለሆንም ይህን ወደኳዋላ ጎታች
ባሕልን መለወጥ መቻል አለበን እላለሁ። ሰው በሰውንቱ መከበር አለበት።

ኤችአይቪ የነጭ ደም ሴል በማጥቃት የሰውነትን የበሽታ መከላከያ አቅም በመዳከም የሲዲፎር
በመባል የሚታውቀውን ሴል ቁጥር (cd4 count) ከ 200 በታች በማድረግ የቫይረሱ መጠን በደም
ውስጥ እንዲጨምር በማድረግ ለሕይወት ኣደገኛ እና ምቹ ግዝ ተባቂ በመባል የሚታውቁትን
በሸታዎች ኦፓርቸንሰቲክ እንፈክሽስ  (Opportunistic infections) OIs. በመፍጠር የኤድስ  
ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደርጋል። ለምሳሌ ያህል ጤነኛ በነበርንበት ጊዜ ከማይተናኮሉን
ባክቴሪያዎች እንደ ኒሞንያ (Pneumonia) አይነት በሽታዎች ያስከትላል። የቆዳ ካንሰር
(Kaposi's Sarcoma) እና የኣንጎል በሽታም ሊኖሩ ይችላሉ። AIDS Related Conditions
(ARC) ወይም ኣርክ የሚባሉ ምልክቶችም ሊመጡ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል የንፍፊት ማበጥ፣
የማይለቁ ትኩሳቶች፣ ድካምና ተቅማጥ፣ ክብደት መቀንስ (ከመጠን በላይ)፣ ደረቅ ሳልና ከባድ
የእንቅልፍ ላብ ይገኙበታል። ትረሽ (Thrush) እና ሽንግልስ (Shingles) የሚባሉ በሽታዎችም
ሊኖሩ ይችላሉ።

ኤችአይቪ እንዳይዘን የምንከላከልበት የክትባት ዘዴ የለም። ኤችአይቪ ከያዘም በኋላ የሚፈውስ
መድኃኒት የለም። በአሁኑ ጊዜ የፀረ-ኤችአይቪ መዳኒት ትልቅ አስተዋጾ በመስጠት ላይ ይገኛል።
ኤችአይቪ እንዴት እንደሚተላለፍ በምርምር የተደገፉ መረጃዎችን በመከታተል ተረድቶ ቫይረሱ
እንዳይሰራጩ ትክክለኛዎቹን ጥንቃቄዎች መከተልና ለሌሎችም ማስተማር የያንዳንዳችን ኃላፊነት
መሆን ይገባል። ኤችአይቪ ኣሰቃቂና ኣደገኛ በሽታ ቢሆንም እንደጉንፋን በቀላሉ የሚተላለፍ
ስላልሆነ ልንከላከለው የምንችለው በሽታ ነው። ስለ ቫይረሱ በጥልቀት ለማወቅ ባንፈልግም እንኳን  
እንዳንያዝ እና እንዴት
እንደምንከላከል መረዳትና ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ እንዴት
እንደምንጠነቀቅ ማወቁ በጣም ጠቃሚ ነው።

ኤችአይቪ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1978 (፲፱፻፸ ዓ.ም.) ወዲህ ሲሆን እስከ 1985 ድረስ
የተበከለ ደም ናሙና በመወጋትና በመሳሰሉት ብዙ ሰዎች ይዚህ ሰለባ በመሆን ብዙ ሰዎች ተይዘዋል።
ከ1988 ወዲህ ግን ኤችአይቪ ሲኖር ደም ውስጥ ነጭ ሴል የሚሠራውን ኣንቲቦዲ (Antibody)
በመመርመር ኤች አይቪ ቫይረስ እንዳለ እና እንደሌለ የሚጣራበት ፈጣን የምርመራ ዘዴ ስለተሠራ
በተለይ የደም ማነስን ለመከላከል ሆስፒታል ከሚሰጠን ደም በመተላለፍ ሊይዝ የሚችለው ቫይረስ
ወደ መጣፋቱ ደርሷል።

ኤችአይቪ ሊተላለፈ የሚችልባቸው መንገዶች ውስጥ ዋነኞቹ ቫይረሱ ያለበት ሰው የተጠቀመበትን
መርፌ በመጠቀም ወይም ኣስፈላጊ ጥንቃቄ ሳይደረግ ለሚፈጸሙ የተለያዩ የግብረ ሥጋ ግንኙነቶች  
ነው።

ኤችአይቪ በሚከተሉት ሁኔታዎች ሊተላለፍ ይችላል

  • ቫይረሱ ያለበት ሰው የተጠቀመበትን የድረግ (Drugs) መርፌ ሌላ ሰው ቢጠቀምበት
    (Intravenous) በቫይረሱ መተላለፍ የተነሳ በበሽታው መያዝ ይቻል ይሆናል።

  • በበሽታው ከተያዘ ወይም ቫይረሱ ካለበት ማንኛውም ሰው (ወንድ ወይም ሴት) ጋር የግብረ
    ሰዶም ግንኙነት (Homosexual, bisexual intercourse) በማድረግ በሽታው ሊይዝ
    ይችላል።

  • ቫይረሱ ወይም በሽታው ካለበት ሰው ጋር በሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት (Heterosexual
    intercourse)  

  • ቫይረሱ ያለባት እናት በሽታውን (ማህፀን ውስጥና በምትወልድበት ጊዜም) ለሕፃንዋ ማስተላለፍ
    (Intrauterine, perinatal) ትችላለች።
    በበሽታው የተያዘች እመጫትን የጡት ወተት በመጥባት (በመጠጣት) ሕፃናትን በሽታው
    ሊይዛቸው ይችላል።

ኤችአይቪ ቫይረስ እንዳይስፋፋ የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ጠቃሚ ነው

  • ከማንኛውም ዓይነት የግብረ ሥጋ ግንኙነት (ከተቻለ) መቆጠብ፣ ወይም ቫይረሱ ካሌለበት
    ኣንድ ታማኝ የፍቅር ጓደኛ በስተቀር ከሌላ ሰው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ኣለማድረግ።

  • ለረዥም ጊዜ ተማምነው ኣብረው የቆዩ ባልና ሚስት መስጋትና ለኤችአይቪ ሲባል በኮንዶም
    (Condom) መጠቀም የለባቸውም። ታማኝነት ከመቼውም ጊዜ ኣሁን ኣስፈላጊ በመሆኑ
    ለትዳሮ ታማኝ ይሁኑ በአሁ ኑሰት ከትዳር በፊት መመርመር ደሞ ሌላኛው አማራጭ ነው።

  • የሚወጉ ድራጎች (እተደበቁ ተሰባስበው ባልፀዱ መሣሪያዎች ከሚወስዱ ጋር) ኣለመውሰድ።
    በሽታው ከያዘው ሰው ጋር መርፌና ሲሪንጋ ኣለመጋራት።

  • ከማያውቁት ሰው ወይም ከብዙ ሰዎች ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በማድረግ ከቆዩ
    (ኣመንዝራ) ጋር ማንኛውንም ዓይነት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ኣለማድረግ

ቫይረሱ እንዳሌለበት ከማያውቁት (ወይም በሽታው ከያዘው) ሰው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ
ካስፈለገ የሚከተሉትን ፬ (አራት) ጥንቃቄዎች መከተል ጠቃሚ ነው፦
(ኣስቀድሞም ግን የኣካባቢውን የሚኖሩበትን የኤች አይቪ--ኤድስ ሕግ ማወቁ በይበልጥ
ጠቃሚ ነው።)

የኤችአይቪ ቫይረስ ያለባቸው የተለያዩ የኣባለ ዘር ፍሳሾች (Semen, vaginal
secretions) ወደ ሌላ ሰው (ብልት፣ ኣፍ፣ ፊንጢጣ ወዘተ...) እንዳይገቡ መጠንቀቅ።

የኤችአይቪ መኖር ካጠራጠረ የግብረ ሥጋው ግንኙነት ከመጀመሩ በፊት ወንድየው የላቴክስ
(Latex) ላስቲክ ኮንዶም ብልቱ ላይ ማድረግ ኣለበት። ከቆዳ (Skin) የሚሠራው ኮንዶም
ዓይነት ከኤችአይቪ አይከላከልም

የላቴክስ ኮንዶም ሲጠቀሙ በተጨማሪም (Lubricant) መጠቀም አይርሱ እንዳይቀደድ
ከመርዳቱም በላ (Lubricant) በውሃ (Water-base) የሚለውን ገዝተው ይጠቀሙ እንጂ
እንደ ቫስሊን የኣሉ ነዳጅ ዘይት (Oil-based) ቅባቶች ኮንዶሙን እንዲቀደድ ስለሚያረጉት
ለመጠቀ ጥሩ ነው። ፓኬቱ ላይ የተጻፈውን ቀን እንዳለፍበት እና እንዳላለፍበት ማንበብ
ያስፈልጋል። ከግብረ ሥጋው ግንኙነት በኋላ ላቴክሱን በጥንቃቄ ማውጣት መረሳት የለበትም።

ኤችአይቪ ቫይርስ በዓለም ላይ(በኢትዮጵያም ጭምር) በመስፋፋት ላይ ስለሚገኝ መጠንቀቅ በጣም
እጅግ አስፈፈላጊ ነው።  ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዬጵያ ውስጥ የኤድስ ታማሚዎች መኖራችው
የተረጋገጠው
በ1978 ዓ/ም ነው።

በተጨማሪም.......
ኤችአይቪ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው (በብዛት) ሊተላለፍባቸው የሚችልባቸውን ቍሳቁሶችን ከማንም
ሰው ጋር አለመዋዋስ። ለምሳሌ ያህል የጺም መላጫ፣ የጥርስ ብሩሽና መፋቂያ የመሳሰሉትን
ኣለመዋዋስ።
ደም ሊያስተላልፉ የሚችሉ ጎጂ ባህሎች እንዲቀሩ ማድርግ
ለምሳሌ፡ የሴት ልጅ ግርዛት፤ እንጥል ማስቆረጥ፤ ጥርስን መንቀስ

ኤችአይቪ ቫይረስ ሊኖርባቸው የሚችሉ ደምና የመሳሰሉትን ጓንት ሳያደርጉ ኣለመነካካት።
ኤችአይቪ ለማያውቁ ማሰማትና ለልጆች ማስተማር (Education) እንዲሁም
ኤችአይቪ ያለባቸውን በሚቻለን ሁሉ የመርዳት ኃላፊነትና በየጊዜው የሚገኙትን የምርምር
ውጤቶች ለማወቅ መሞከርና
ዕውቀቱን ማሰራጨት ኣለብን
ኤችአይቪ ቫይረስ ደካማ በመሆኑ ከሰወነት ውጭ ለረዥም ጊዜ ኣይቆይም።

አንድን ሰው ቫይረሱ እንደሌለበት ለማወቅ የተለያዩ (ተደጋጋሚ) የደም ምርመራዎች በማድረግ
ማወቅ ይችላል።
ኤችአይቪ በመጨባበጥና፣ በመሳሳም፣ እንዲሁም በሽንትና በሰገራ፣ በወባ ትንኝና ቁንጫን በመሳሰሉት
ደም መጣጮች ነብሳት ኣይላለፍም።
የኤይችአይቪ ቫይረስ (እራሱን ስለሚቀያይር) ጥሩ ዓይነት የመከላከያ ክትባት ለማገኘት በጥናት ላይ
የገኛል።  ቫይረሱን መግደል በጣም ከባድ ስለሆነ (የኤችአይቪ ቫይረስ ከሰው ጂን ጋር ስለሚደበቅ)
ፈዋሽ መድኃኒት ማገኘቱ አስቸጋሪ ሆኖ ሳለ በአሁኑ ግዜ የፀረ-ኤይችአይቪ መዳኒቶች ትልቁን ሚና
በመጫወት ላይ የገኛል።    

Antiretroviral Therapy (ART) drugs የፀረ-ኤይችአይቪ መዳኒቶች ቫይረሱ ሰውነት
ውስጥ እንዳይባዛ  በመከላከል ጤንነትን እየጠበቀ መኖር የሚያስችል መዳኒት ነው። ኤችአይቪ
እንዳለበት አንድ ሰው ካረጋገጠ በጥሩ ጤንነት ለመኖር መሞከርና የተመጣጠነ ምግብ በመመገብና
እራሱን በመጠበቅ መኖር ይቻለል። ተመርምሮ እራስን ማወቅ ብዙ ጠቀሜታ አለው። የኤችአይቪ
ቫይረስ በሰውነት ውስጥ ሳይበዛ እና ብዙ ጉዳት ሳይጀምር ማወቁ ትልቅ ጠቀሜታ አለው። መዳኒት
ቶሎ መጀመሩና እራሱ ለጤና ትልቅ ልዩነት ስላለው አውቆ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ አዋቂነት
ነው። አንዴ የፀረ-ኤይችአይቪ መዳኒት ከተጀመረ በሃላ ማቁዋረጥ አይቻልም ካለ ዶክተሮዎ ትዛዝ
በስተቀር።

ኤችአይቪ ሁሌ በመካከላችን ስላለ በኤችአይቪ ላለመያዝ የቻልነውን ያህል አስታውጾኦ ማርግ
ይጠበቅብናል። ዋነኛውና ሳይጠቀስ መታለፈ የሌለበት የራሳችን እርምጃ ወስድ ነው መመርመር።
በአሁኑ ሰአት
በኢትዮጵያ ውስጥ 1.3 ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ሰዎች ከኤችአይቪ ቫይርስ ጋር
አብረው ይኖራሉ። በዓለም ላይም
ከ 25 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኤድስ በሚመጣ በሸታ
ተይዘው ሞተዋል።  በ
2006ዓ/ም ወደ 2.9 ሚሊዮን የሚጠጉ ወንዶች፤ ሴቶች እና ሕጻናትም
ሕይወታቸውን አተዋል። ኤችአይቪ ከተያዙት ውስጥ ከግማሸ በላይ የሚገምቱት ሲሞቱ
39.5
ሚሊዮን የሚሆኑ ከቫይርሱ ጋር በመኖር ይገኛሉ። በቅርቡ በ
UNAIDS/WHO እንደተዘገበው 4.3
ሚሊዮን የሚጠጉ አዲስ ሰዎች በኤችአይቪ እንደተያዙ ይገልጻል።  መላው የዓለም ሕዝብ በጣም
የጠነከረ ጥንቃቄ ማድረግ ካልጀመረ በቫይረሱ የሚያዘው ሰው ቍጥር በየዓመቱ እጥፍ እየሆነ
ሊቀጥል እንደሚችልና ለማስታመምም ብዙ ብሊዮን ዶላርስ እንደሚያስፈልግ ተገምቷል። የግብረ
ሰዶም ግንኙነት የሚያደርጉ እና ድራግ የሚወጉ ሰዎች ብቻ ነው የሚይዛቸው እየተባለ ቸል ሲባል
ቆይቶ ኣሁን ግን የሁላችንም ፀር በመሆኑ የሚፈለግብንን አላፊነት ብንወጣ ተገቢ ነው።
ከመንግሥታትም ጋር በመተባበር ባይረሱን ለመቆጣጠር (Control) መሞከር ጥሩ ነው። የፈንጣጣን
በሽታ ከዓለም ለማጥፋት (Eradication) ከጠቀሙን መካከል ክትባትና የሕዝቡ ትብብር ዋናዎቹ
ናቸው። ስለ ግብረ-ሥጋ ግንኙነት (Sexual) በግልጽ ማውራት ለማንኛውም ሕብረተሰብ ኣሳፋሪ
ቢሆንም የኤችአይቪ/ኤድስ ያመጣብን ዱብ-ዕዳ የሕይወት ጉዳይ ስለሆነ በግልጽ መወያየት አለብን።

ይህ ጽሑፍ የተጻፈው የሕክምና ዕርዳታ ለመስጠት ኣይደለም። በበለጠ ለመረዳት ሓኪሞቻችሁን
ኣማክሩ።
  • ከአንድ ብርቱ ሁለት መዳኒቱ ነውና አብረን በመስራት ወገን እናትርፍ!
This site contains
Ethiopic text.
Without
rendering
support, you may
see question
marks, boxes or
other symbols
instead of Ethiopic
characters.
ኤችአይቪ-ኤድስ
Writtien by Abesha Care
See also  Antiviral drug
References
1, Dr. Aberra Molla in the March and April, 1991 G.C
2.
UNAIDS/WHO 2006 Report on the global AIDS epidemic
AMHARIC PAGE
© 2007 - 2008 Abesha Care Inc.  All Right Reserved. office@abeshacare.org